ፍትሀዊ የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብቶችዎን ይወቁ

Front of postcard reads, "የፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት መብቶችዎን ይወቁ በአገር አቀፍ ደረጃ፣ በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ተመርኩዞ በመኖሪያ ቤት ጉዳዮች ላይ አድልዎ ማድረግ ህገ ወጥ ነው፥ • ዘ ር • ሃይማኖት • የቤተሰብ ሁኔታ • ቀ ለ ም • የአካል ጉዳት ሁኔታ • የመጡበት አገር • ጾታ በሚኖሩበት ከተማ ወይም ስቴት ተጨማሪ ጥበቃዎች ሊኖሩ ይችላሉ። በመኖሪያ ቤት ጉዳዮች ላይ የተፈጠረን አድልዎ ለእኩል መብቶች ማዕከል ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ ከስር ያለውን የ QR ኮድ ስካን ያድርጉ። 202-234-3062. info@equalrightscenter.org. equalrightscenter.org."  Back of postcard reads, "የቤት አከራይ የሚከተለውን አድርጓል ብለው ያስባሉ፥ በዘርዎት ምክንያት ከሌሎች በተለየ ሁኔታ አስተናግዶዎት? ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሞብዎት? በቤተሰብዎ መጠን ምክንያት ቤት አላከራይም ብሎዎት? የመኖሪያ ቤት ቫውቸር ስላለዎት ከልክሎዎት? ማንኛውንም የመኖሪያ ቤት መገለል ለማሳወቅ የእኩል መብቶች ማዕከልን ያነጋግሩ።"

ለአካባቢ ሸማቾች ስለ ፍትሀዊ የመኖሪያ ቤት መብቶቻቸው በተመለከተ ያዘጋጀነው ይህን አዲስ የመረጃ ምንጭ ስናካፍልዎ በደስተኝነት ነው። ድርጅትዎ ለማህበረሰብዎ ለማከፋፈል የሚፈልግ ከሆነ የመረጃውን የወረቀት ግልባጮች እንሰጥዎታለን። ኮፒዎችን ለመጠየቅ በcommunications@equalrightscenter.org. የኢሜይል መልዕክት ይላኩ።

በአገር አቀፍ ደረጃ ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሄራዊ ማንነትን፣ ሀይማኖትን፣ አካል ጉዳተኝነትን፣ ጾታን ወይም የቤተሰብ ደረጃን (በቤተሰቡ ውስጥ የልጆች መኖርን ይገልጻል) መነሻ መሰረት በማድረግ በመኖሪያ ቤት ላይ የማግለል ድርጊት መፈጸም ህገወጥ ነው። እነዚህ ባህሪያት ‹‹ጥበቃ የሚደረግላቸው ምድቦች›› ተብለው ይጠራሉ። ጥበቃ የሚደረግለት ምድብ ማለት በህጉ ስር ከመገለል ጥበቃ ለማግኘት ብቁ የሆኑ ሰዎች ናቸው። በፌደራል ደረጃ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሰባት ምድቦች በተጨማሪ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚከተሉትን መነሻ በማድረግ በመኖሪያ ቤት ላይ ማግለል ህገወጥ ነው፡

  • እድሜ
  • የጋብቻ ሁኔታ
  • ጾታዊ ምርጫ
  • የጾታ ማንነትና አገላለጽ
  • የገቢ ምንጭ
  • የቤት ውስጥ ጥቃት፣ የወሲባዊ ጥቃትና ትንኮሳ ደረጃ
  • የቤተሰብ ኃላፊነቶች
  • የፖለቲካ አመለካከት
  • የግል ገጽታ
  • የመግቢያ ፈተና
  • የመኖሪያ/ስራ ቦታ

በሜሪላንድ ተጨማሪ የሚከተሉትን መሰረት ላደረገ ማግለል የሚደረጉ ግዛት አቀፍ ጥበቃዎች አሉ፡

  • የጋብቻ ሁኔታ
  • ጾታዊ ምርጫ
  • የጾታ ማንነት
  • የገቢ ምንጭ

በቨርጂኒያ ተጨማሪ የሚከተሉትን መሰረት ላደረገ ማግለል የሚደረጉ ግዛት አቀፍ ጥበቃዎች አሉ፡

  • አረጋዊነት (55+)
  • ጾታዊ ምርጫ
  • የጾታ ማንነት
  • የገቢ ምንጭ
  • የዘማችነት ደረጃ

እርስዎም ማየት እንደሚችሉት በDMV ክልል ውስጥ በመኖሪያ ቤት ላይ ለሚፈጸም ማግለል የሚደረጉ በመጠኑ ውስብስብ የጥበቃ ስራዎች አሉ። በማህበረሰብዎ ላይ የትኞቹ ጥበቃዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ በተመለከተ የትኛውም ጥያቄዎች ካሉዎ እባክዎ ያነጋግሩን!

የፍትሀዊ የመኖሪያ ቤት ህጎች ከመኖሪያ ቤት ጋር ተያያዥነት ካላቸው ግብይቶች ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ተግባሮች ይከለክላል፡

  • የአንድን ሰው የጥበቃ ምድብ አባልነት መነሻ በማድረግ መኖሪያ ቤት ለማከራየት ወይም ለመሸጥ ፍቃደኛ አለመሆን።
    • ለምሳሌ፡ ለአንድ አመልካች የኪራይ ክፍያውን ለመክፈል የመኖሪያ ቤት ፋክቱር የሚጠቀም በመሆኑ ምክንያት መኖሪያ ቤት ለማከራየት ፍቃደኛ አለመሆን የገቢ ምንጭን መሰረት ያደረገ ማግለል ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።
  • የአንድን ሰው የጥበቃ ምድብ አባልነት መነሻ በማድረግ አግላይ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎችን ተግባራዊ ማድረግ።
    • ለምሳሌ፡ ህጻናት ከሌሉት አመልካች ቤተሰብ ይልቅ ህጻናት ካሉት አመልካች ቤተሰብ ከፍተኛ የዋስትና ተቀማጭ መጠየቅ የቤተሰብ ደረጃን መሰረት ያደረገ ማግለል ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።
  • አግላይ ምርጫን ማስተዋወቅ
    • ለምሳሌ፡ የማስታወቂያው ‹‹ለተመራጭ ጥንዶች ተስማሚ አፓርታማ›› ብሎ መግለጽ የቤተሰብ ደረጃን መሰረት ያደረገ ማግለል ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።
  • የአንድን ሰው የጥበቃ ምድብ አባልነት መነሻ በማድረግ የሚፈጸም መገኘትን ማሳሳት
    • ለምሳሌ፡ ለጥቁር እጩ ተከራይ ምንም የሚከራይ አፓርታማ እንደሌለ በመንገር ለነጭ እጩ ተከራይ የሚከራይ አፓርታማ መኖርን መንገር።
  • መዝጋት
    • በታሪክ መንገድ መዝጋት የሪል ስቴት ሙያተኞች በነጭ የቤት ባለቤቶች ላይ መኖሪያ ቤታቸውን ከገበያ ዋጋ ባነሰ ዋጋ እንዲሸጡ ጫና ለማሳደር አላማ ጥቁር ነዋሪዎች በቅርቡ ወደ መኖሪያ መንደራቸው ሊመጡ እንደሆነ በመንገር እንዴት የዘረኝነት ፍራቻ እንደሚፈጥሩባቸው ይገልጻል። ይህ በ1950ዎቹና 1960ዎቹ ለነጮች መኖሪያ ከተሞቻቸውን ለቀው እንዲሄዱ እና ለመኖሪያ መንደር መነጠል አስተዋጽኦ አድርጓል። እጅግ ዘመናዊ የመንገድ መዝጋት አይነቶች የሪል ስቴት ሙያተኞችን ወደ መኖሪያ መንደር የሚገቡ የፋክቱር ያዦች ላይ ይህ እውነት ባይሆንም እንኳ የሚፈጸም ምርጫን ሊይዝ ይችላል።
  • መቀስቀስ
    • መቀስቀስ የመኖሪያ ቤት አቅራቢ እጩ ተከራይ ወይም ገዢን ከተወሰኑ መኖሪያ መንደሮች ወይም መኖሪያ ቤቶች ጥበቃ የሚደረት ምድብ አባልነትን መነሻ በማድረግ ወደ ሌላ ቦታ በሚመራበት ወቅት ነው። ለምሳሌ፡ ለላቲን አሜሪካ ቤት ፈላጊ ቤተሰብን በመኖሪያ መንደሩ ውስጥ ብዙ የላቲን አሜሪካ ቤተሰብ ነዋሪዎች ወዳሉበት መንደር የሚመራ የኪራይ ወኪል ወይም የሪል ስቴት ወኪል ብሄራዊ ማንነትን መሰረት ያደረገ ማግለል እንደፈጸመ ሊቆጠርበት ይችላል።
  • ትንኮሳ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ ወይም ማስገደድ
    • ለምሳሌ፡ አንድን ተከራይ ወሲባዊ ድርጊት ካልፈጸመ በቀር መኖሪያ ቤትን ለማደስ ፍቃደኛ አለመሆን ወሲባዊ ትንኮሳ ተደርጎ ይቆጠራል።
  • በቀል
    • ለምሳሌ፡ አንድን ተከራይ ለአከራይ የመኖሪያ ቤት መገለል ቅሬታ በማቅረቡ ምክንያት ከቤቱ ለማፈናቀል መሞከር።
  • የትኛውም ሌላ መኖሪያ ቤት እንዳይገኝ የሚያደርግ ወይም የሚከለክል ምግባር፡
    • ለምሳሌ፡ ለአካል ጉዳተኛ ተከራይ ተደራሽ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆን። ለአካል ጉዳተኛ ተከራይ ተደራሽ የመኪና ማቆሚያ ቦታ መስጠት ‹‹አሳማኝ አገልግሎት›› የመስጠት ምሳሌ ማለትም ለአካል ጉዳተኛ ሰው መኖሪያ ቤቱን እኩል የመጠቀምና የመደሰት እድል ለመስጠት በመኖሪያ ቤት አቅራቢ ህግ፣ ፖሊሲ፣ አሰራር ወይም አገልግሎት ላይ የሚደረግ ለውጥ፣ ልዩ ሁኔታ ወይም ማስተካከያ ምሳሌ ነው። ‹‹አሳማኝ አገልግሎት›› አሁን ባለ መኖሪያ ቤት፣ በአካል ጉዳተኛ በተያዘ መኖሪያ ቤት ላይ አካል ጉዳተኛውን መኖሪያ ቤቱን በተሟላ ሁኔታ እንዲጠቀም ለማስቻል የሚደረግ መዋቅራዊ ለውጥ ነው። ለአንድ ግለሰብ አሳማኝ አገልግሎት ወይም መሻሻያ አለማቅረብ አካል ጉዳትን መሰረት ያደረገ ማግለል ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።

በመኖሪያ ቤት ላይ ማግለል ተፈጽሞብኛል ብለው ካመኑ የእኩል መብቶች ማዕከልን ማናገር ይችላሉ። የደረሰብዎን አጋጣሚ ሪፖርት ለማድረግ በስልክ ቁጥር 202-234-3062 ይደውሉ ወይም በinfo@equalrightscenter.org. የኢሜይል መልዕክት ይላኩ።

———

ERC Logo

Start typing and press Enter to search